Loading..

አባይ ወንዝ ድልድይ ወደ ብልጽግና ጉዞ መሻገሪያ አዲስ የታሪክ አሻራችን ነው ፡፡

የከተማውን ሁለት ክፍሎች በበቂ ሁኔታ የሚያገናኝ

የተጋገረ ድልድይ ግንባታ ላይ

ስለ አባይ ወንዝ

በገመድ የተወጠረው የባህርዳር ወንዝ ድልድይ በሊድዌይ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት ሲመራ መገኛውም በባህርዳር ከተማ በአባይ ወረዳ በብሉ ናይል

ተጨማሪ ያንብቡ

ምን

የአባይ ወንዝ ድልድይ በአይነቱ ፣ በውበቱና በዘመናዊነቱ በሀገራችን ቀዳሚ የሆነ በገመድ ላይ ተወጣሪ የድልድይ ዓይነት ነው ፡፡ ድልድዩ ሁለት ተሸካሚ ማማዎችን (ውቅሮች) እና በማማዎቹ መካከል ሶስት ክፍሎች (span ) አሉት ፡፡ ድልድዩ 380 ሜትር ይረዝማል ፡፡ የጎን ስፋቱ ደግሞ 43 ሜትር ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ግዜ 6 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ባለሁለት አቅጣጫ የብስክሌት ተጠቃሚዎች መስመር እንዲሁም 5 ሜትር የእግረኛ መሄጃን ያካተተ ነው ፡፡

የት

የአባይ ወንዝ ድልድይ የሚገኘው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ ከተማ በባህርዳር ነው ፡፡ በከተማዋ ካለው ከጣና ሃይቅ በታችኛው ተፋሰስ በ3.38 ኪ.ሜ እርቀት ላይ ይገኛል፡ ፡ የድልድዩ ስፍራ በአቅጣጫ መጠቆሚያ ጂፒኤስ መሰረት E11 ° 25 '15 .47 "፣ N 37 ° 24 '29 .67" ላይ ያመላክታል ፡፡

መቼ

የባህርዳር አባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት የተጀመረው ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ. ም ነው ፡፡ የግንባታ ስራው የሚጠናቀቀው ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው ፡፡




ወጪ

የአባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ወጪ 1,437,000,000 ብር ወይም በዶላር 51.34 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው ፡፡ የፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት ይሸፈናል፡፡

ለምን

• በባህርዳር ከተማ የዛሬ 60 አመት ገደማ የተገነባው ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ ከአገልግሎት ብዛት ፣ ጥበት፣ ከእድሜው መርዘም እና በመስመሩ እየጨመረ ከመጣው የትራፊክ ፍሰት አንጻር ተደጋጋሚ ጉዳቶች ሲገጥሙት በመቆየቱ አዲስ ድልድይ መገንባት አስፈልጓል፡፡

• ከግብፅ ካይሮ ተነስቶ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ድረስ የሚዘልቀውና 10 ሺ ኪ.ሜ የሚረዝመው የታላቁ የትራንስ አፍሪካ አካል በመሆኑ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅምን በሚመጥን መልኩ ደረጃውን የጠበቀ ድልድይ መገንባት ተገቢ በመሆኑ ፡፡

• ብዙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ላላት ባህርዳር እና አካባቢዋ አዲሱ ድልድይ እራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ በመሆንና ለባህርዳር ከተማ ውበትን በመጨመር ረገድ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ፡፡

ዜና

የአባይ ወንዝ ድልድይ