Loading..

ዜና

ኢትዬጵያ በአማራ ብሄራዊ ክልል በባህር ዳር ከተማ በአባይ ወንዝ ላይ ረጅሙን ድልድይ መገንባት ጀመረች

አርብ በተደረገው የመክፈቻ ዝግጅት ወቅት የክልሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እና የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ተገኝተዋል ፡፡ባለሶስት መስመር የመኪና መንገድ ፣ የብስክሌት መንገድ እና የእግረኛ መንገድ ያካተተው ይህ ድልድይ 43 ሜትር ስፋት ያለው ነው፡፡ መንግሥትንም ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚጠጋ ወጪ ያስወጣል ተብሎ ይገመታል፡፡ የክልሉ ሚዲያም ፕሮጀክቱ ለማጠናቀቅ ሦስት ዓመታት እንደሚወስድ ገልጿል ፡፡ ዲዛይንና ግንባታውን የሚያካሂደው የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲ.ሲ.ሲ.ሲ) ነው፡፡ የባህር ዳር አባይ ድልድይ ሲጠናቀቅ በኢትዮጵያ ውስጥ ረጅሙ ድልድይ ይሆናል። ይህም በሀገሪቱ ውስጥ አንደኛ የነበረውን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2006 የተከፈተውን የ319 ሜትር የባሺሎ ወንዝ ድልድይ ፤ ሁለተኛ የነበረውን በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የሚገኘውን 305ሜ የሚረዝመው የባሮ ወንዝ ድልድይ እና ሶስተኛ የነበረውን 303ሜ ርዝመት ያለው የአባይ ድልድይን በመብለጥ ነው።




Go Back